Welcome to Nifas Silk Lafto Subcity Peace and Security Office!       እንኳን ወደ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ክ/ከተማችን በህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፤ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ለኑሮ፣ ለስራ እና ለመዝናኛ ተመራጭ እንድትሆን ይተጋል!
image
image
image
image
image

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ የግል ጥበቃ ኤጀንሲ አባላት እና ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ጥበቃዎች ስልጠና ተሰጠ

ታህሳስ 11, 2018
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ለግል ጥበቃ ኤጀንሲ አባላት እና ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ጥበቃዎች ስልጠና ሰጥቷል። ስልጠናው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በትብብር የተዘጋጀ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ አቶ ጌታሁን አበራ የከተማውን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ለማድረግና ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን ማህበረሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ ይገባል ብለዋል። ህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ከመደበኛ የፀጥታ አካሉ ጋር ተቀናጅተው ከመስራት ባሻገር ዘመናዊ ቴክኖሎጂ (ሲሲቲቪ ካሜራ) በመጠቀም የወንጀል ምጣኔን መቀነስ እንደሚገባ ተናግረዋል። የሰላምና የፀጥታ ጉዳይ ለመንግስት ብቻ የሚተው አይደለም ያሉት አቶ ጌታሁን የግል የጥበቃ ኤጀንሲዎችም የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ አካባቢያቸውን በንቃት መጠበቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጄ ድሪብሳ አንዳንድ የጥበቃ ኤጀንሲዎች የተቋቋሙበትን ዓላማ ወደ ጎን በመተው ከቀጠሯቸው የጥበቃ አባላት መካከል በሌላ እኩይ ተግባር ላይ እየተሰማሩና ወንጀሎች እየተፈፀሙ በመሆኑ ኤጀንሲዎች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል። ያለ በቂ ዋስትና ቅጥር መፈፀም እንዲሁም የአንድ አከባቢ ሰዎችን በጥበቃ ስራ ላይ ማሰማራት ለወንጀሉ መባባስ ዋነኛ ምክንያት መሆኑንም አንስተዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ኃላፊ ኮማንደር ጌታቸው አለነ ወንጀሎችን አስቀድሞ መለየትና መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ በተለይም በመኖሪያና በስራ አካባቢዎች የሚደረጉ ጥበቃዎችን ይበልጥ እያጠናከሩ መሄድ እንደሚገባ ተናግረዋል። የጥበቃ ኤጀንሲዎች ከሰራዊቱ በጡረታና በክብር የተቀነሱና በፀጥታ ስራ ላይ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መሆኑን ጠቅሰው ይህን ልምድ ተጠቅሞ በተቋማት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን መቀነስ ይገባል ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች