Welcome to Nifas Silk Lafto Subcity Peace and Security Office!       እንኳን ወደ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ክ/ከተማችን በህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፤ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ለኑሮ፣ ለስራ እና ለመዝናኛ ተመራጭ እንድትሆን ይተጋል!
image
image
image
image
image

ከበዓላት ጋር በተያያዘ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሬ እንዳይከሰት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

መስከረም 4, 2018
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከመጪው አዲስ ዓመት በዓል ጋር በተያያዘ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሬ እንዳይከሰት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል። የኑሮ ውድነትና ገበያ ማረጋጋት ግብረ ሃይል በዛሬው ዕለት በበዓላት ወቅት ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሬን መከላከል የሚያስችል ውይይት አካሂዷል። በዚህም በዓላቶች ላይ ሊፈጠሩ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ የዋጋ ጭማሪ፣ የገበያ አለመረጋጋት፣ መሰረታዊ ፍጆታዎችን በሚደብቁ ነጋዴዎች፣ የእሁድ ገበያና ሸማች ማህበራት ላይ በስፋት ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ የሚያሳዩ ነጥቦች ተነስተዋል። የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጄ ዲሪብሳ የገበያ ማረጋጋትና የኑሮ ውድነት የሚቀንሱ ስራዎችን ስንሰራ ለበዓላትና ለአንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ቀጣይነት ያለው ስራ መስራት ይገባል ብለዋል። አቶ ደረጄ አክለውም በዓላቱን ምክንያት በማድረግ ሊከሰት የሚችል የዋጋ ጭማሬን ከመከላከል ባሻጋር ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ችግሮችን በተገቢው ለይቶ በቅንጅትና በትብብር መስራት ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መኮንን ዘነበ በመጪው መስከረም ወር ተከታታይ በዓላት በመኖራቸው ይህን ተከትሎ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የአቅርቦት ችግርና የዋጋ ጭማሬ እንዳይከሰት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ አንፃር ከሸማች ማህበራት፣ ከአርሶ አደሮች፣ ከጥቃቅን አንቀሳቃሾች፣ ከአቅራቢዎችና ከአምራቾች ጋር በቅርበት በመስራት በእሁድ ገበያ መዳረሻ ስፍራዎችና በባዛሮች ላይ ምርቶች በስፋትና በጥራት ቀርበው ገበያውን እንዲያረጋጉ እየተደረገ ነው ብለዋል። በመጨረሻም ቀጣይ የሚከበሩ በዓላት ጋር ተያይዞ ስለሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ የስራ አቅጣጫ ተቀምጧል።

መልዕክትዎን ይላኩ