Welcome to Nifas Silk Lafto Subcity Peace and Security Office!       እንኳን ወደ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ክ/ከተማችን በህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፤ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ለኑሮ፣ ለስራ እና ለመዝናኛ ተመራጭ እንድትሆን ይተጋል!
image
image
image
image
image

ለ6ኛ ኮርስ ለአዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ተሰጠ።

ህዳር 28, 2018
ላፍቶ፣ ታህሳስ፣ 21/2018:- በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ለ6ኛ ኮርስ ለአዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት የንድፈ ሃሳብ ስልጠና ሰጥቷል። በእለቱም የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና የፀጥታ አካላት እንዲሁም አዲስ ምልምል ሰላም ሰራዊት አባላት ተገኝተዋል። የንድ ሃሳብ ስልጠናው የሰላም ምንነትና ሃገር ወዳድነት የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት ደንብና መመሪያ እንዲሁም ወንጀል መከላከል በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው። መርሃ-ግብሩን ያስጀመሩት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ ባለፉት ዓመታት የሰላም ሰራዊት አባላት በክፍለ ከተማው የሚከናወኑ የተለያዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የበጎ ፍቃድ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ እያደረጉ ያለው ተሳትፎ የጎላ መሆኑን አንስተዋል። ከዚሁ ተግባር ጎንለጎን የሰላም ሰራዊት አባላት ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የአካባቢውንና የህብረተሰቡን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ በርካታ ስራዎች መስራታቸውን ገልፀዋል። የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጄ ድሪብሳ የአዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት በንድፈ- ሃሳብና በመስክ የሚሰጠውን ስልጠና ስነ-ምግባር በተሞላበት ሁኔታ በመከታተልና አቅማቸውን ማጎልበት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ስልጠናው ለ10 ቀናት የንድፈ ሃሳብና የመስክ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ገልፀው የተሰጣቸውን ሰላም የማስጠበቅ ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ኃላፊ ኮማንደር ኪዳኔ አያና አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት ለፀጥታ አካላት አጋዥ ሃይል በመሆን የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ሃገራዊ ሃላፊነቱን መወጣት አለበት ሲሉ ተናግረዋል። የ6ኛ ኮርስ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት በበኩላቸው የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው ለፀጥታ ስራው ተደማሪ አቅም እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ